ድንገተኛ ሁኔታዎችን እና አደጋዎችን በደንብ መቋቋም

የቤተሰብን መሰረታዊ ቅድመ ዝግጅት ጠያቂ ነው፡፡ ምን ማድረግ እንዳለባችሁ እንዴት ታውቃላችሁ?

ውድ ነዋሪዎች:

ለተፈጥሮ አደጋ ወይም ለድንገተኛ ሁኔታዎች በእርግጥ ዝግጁ ነን?

የሃይፋ ከተማ ባለፉት አስር ዓመታት እውነተኛ ለውጥ እያለፈች እና በዚህ መስክ ውስጥ የመሪነት ደረጃ አላት:: በእነዚህ ዓመታት ውስጥ ብዙ እውቀት እና ልምድ ሸምተናል:: ለናንተ ቤቶች እና ቤተሰቦች ለማዘጋጀት ይረዳቸዋል በማለት በዚህች መጽሔት ያሰፈርነውን የልምድ ምክር ከእናንተ ጋር ለማጋራት በማሰብ ነው::

በ 6 ኛው ወር 2019 በኪኔሬ አካባቢ ተደጋጋሚ መጠነኛ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ ነበር፡ አልፎ አልፎም በአንዳንድ የትምህርት ማእከል በሚገኙ የመሬት መንቀጥቀጥ ማስጠንቀቂያ ጣቢያዎች ተመዝግቧል፡፡ ይህም በክልሉ ውስጥ ባሉ አካላት እና ድርጅቶች ውስጥ የተቀናጁ ተነሳሽነት እና መፍትሄዎችን ለማስተባበር ልዩ አስቸኳይ ጉባኤን እንድናካሂድ አስስገድዶናል፡፡

በብዙ የዓለም አካባቢዎች ውስጥ ከተከሰቱ አደጋዎች በተገኙ ልምዶች ጋር፤ የዜጎች የመሬት መንቀጥቀጥ ከመከሰቱ በፊት፤ በወቅቱ እና ከዚያ በኋላ በዜጎች የተያዙ እርምጃዎች በህይወት እና ንብረት ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ ከፍተኛ ተጽዕኖ አለው፡፡ ከዚህ መረዳት እንደሚቻለው የሃይፋ የማዳን እና የነፍስ አድን ቡድን በአሁኑ ወቅት እየተገነባ ሲሆን በከተማይቱ በሚገኙ በጎ ፈቃደኞች የተካተቱ በአደገኛ እና በአደጋ ወቅት አስቸኳይ ድጋፍ ለማበርከት፤ ባለሙያ ኃይል እስኪመጣ ድረስ ህይወትን ለማትረፍ እና አደጋዎችን ለመወጣት እንዲሁም ተጨማሪ ኃይል ይሆኑ ዘንድ፤የከተማው ቀ. ይ .ድ.(ቀዳሚ ይእራስ ድጋፍ) ይሆናሉ፡፡

ምን ማድረግ እንዳለባችሁ የሚረዱ 5 ምክረ ነጥቦች

1. "ሐይፋ በእጣት ንኪት" የተሰኘውን አፕሊኬሽን መተግበሪያ ያውርዱ::

ለድንገተኛ መመሪያዎች ለማግኘት (በሞባይል push)

2. መሰረታዊ የሆኑ ምግቦችን አዘጋጁ:

2-3 የሚሆኑ የሚኒራል የታሸገ ውኃ: የታሸገ ደረቅ ማብሰል የማይጠይቅ ምግብ: (የታሸጉ የተለያዩ ምርቶችን: የሕፃናት ምግብ)

3. ለድንገተኛ የኤሌክሪትሪክ ኃይል መቋረጥ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን አዘጋጁ:

 • የተሞላ ለድንገተኛ ጊዜ መብራት
 • የእጅ ባትሪ ከተጨማሪ የባትሪ ድንጋይ ጋር
 • የብዙኃን መገናኛ ትራንዚስተር ሬዲዮ ከነባትሪው (ከትርፍ ባትሪዎች ጋር) የሚዲያ ዘዴዎች ቴሌቪዥን: ኮምፒውተር ወዘተ::
 • የሞባይል ስልክ ከተንቀሳቃሽ ባትሪ መሙያ እና መጠባበቂያ ባትሪ
 • መድሃኒቶች እና የመጀመሪያ እርዳታ መለገሻ
 • መደበኛ ትቅል ናይለን (የተሰነጣጠቁ መስኮቶችን ማተሚያ)
 • የግል እና የጋራ የደህንነት መጠለያዎች ክፍሎችን (ሚቅላጥ/ማማድ) በጥሩ ሁኔታ ማዘጋጀት

4. ለምድር መንቀጥቀጥ አደጋ አጋጣሚ አስፈላጊ መሳሪያዎችን አዘጋጁ:

 • ለበርካታ ቀናት የሚሆን የግል ቁሳቁሶችን በከረጢት ማዘጋጀት
 • የቤተሰብ እና የድንገተኛ ድርጅቶች ስልኮች ዝርዝር ማዘጋጀት
 • የህክምና ሰነዶችን እና የመታወቂያ ካርድ ኮፒ ማዘጋጀት

5. በድንገተኛ ጊዜ አንድ የበራ ሞባይል ስልክ ብቻ አስቀሩ::

የሌሎች የስልክ ባትሪዎች የረዥም ጊዜ የመብራት መቋረጥ አጋጣሚ ያገለግሉዋችኋል:: የሞባይል ባትሪዎችን ሰባስቡ ለአስፈላጊ ጊዜ ይሆናሉ::

ቤትን እና ቤተሰብን ለድንገተኛ ሁኔታዎች አዘጋጁ

አስተውሱ! የተለያዩ ሰዎች ለተለያዩ አጋጣሚዎች በተለያዩ መንገዶች ሃሳባቸውን ይገልጻሉ: በድንገተኛ ወቅትም የሚሰጡ መልሶችና ሃሳቦች እንደ መደበኛ ጊዜ መታየት አለባቸው::

 • ቤተሰባችሁ በሙሉ የደህንነት መጠለያዎችን እና (ሜርሃቭ ሙጋን) የማምለጫ መስመሮችን ማወቃቸውን ያረጋግጡ::
 • አስቀድመው ከድርጊቱ ቦታ ውጭ የመገናኛ ቦታ እና የቤተሰብ ተወካይ ይምረጡ
 • የመጀመሪያ እርዳታ ጥናት አጥንው በቤታችሁ የመጀመሪያ እርዳታ መስጫ መሳሪያ ይያዙ
 • የቤተሰብ ለድንገተኛ ወቅት የሚሆኑ ማህደረ ቁሳቁሶችን እንደሚከተለው ያዘጋጁ:
 • የመገናኛ ዘዴወች: ሬዲዮ ከባትሪ ጋር/ ቴሌቪዥን/ ኮምፒዩተር ከኢንተነት ጋር
 • የመጀመሪያ እርዳታ መስጫ እና መድሃኒቶች
 • የክሬዲት ካርድ መረጃ + የጥሬ ገንዘብ
 • የቤት እና የመኪና ትርፍ ቁልፎች
 • የታተሙ የምግብ ጣሳዎችን መክፈቻ
 • ፊሽካ (የእርዳታ መጥሪያ የሚያገለግል)
 • የእጅ ባትሪ እና የባትሪ ድንጋይ / ለድንገተኛ ወቅት መብራት
 • ሻማ እና ክብሪት / ሲጋራ ማቃጠያ
 • የሞባይል ስልክ ከነመሙያው
 • ስሜታዊ ትርጉም ያለው ተፈላጊ ቁሳቁስ
 • የታሸገ ምግብ እንደ ተታተሙ ጣሳዎች የሚቆረጠሙ ዓይነት
 • ውሃ - ለአንድ ሰው 4 ሊትር ውሃ ለአንድ ቀን (ለ 3 ቀናት የሚሆን)
 • አስፈላጊ ሰነዶች(ኮፒ አድርጎ ከቤት ውጭ ማስቀመጥ እና ዲጂታል ሚዲያ ጨምሮ)
 • የኩፓት ሆሊም ካርድ ኮፒ
 • የመታወቂያ ካርዶች የመንጃ ፈቃድ ጨምሮ ኮፒ
 • የመድኃኒት መግዣ ፈቃድ ሰነዶች
 • አስፈላጊ የስልክ ቁጥሮች ዝርዝር
 • ማተሚያ፡ ሰፋፊ ናይሎን፤ ችድንገተኛ መስኮቶች የፈነዱ እንደሆነ መሸፈኛ
 • የእሳት ማጥፊያን (ችፎቆች)
አስታውሱ! ከእናንተ አንዱ መሣሪያዎችን በየወቅቱ በየ ሦስት ወር የሚፈትሽ ሃላፊ አድርጉ (ውኃውን መቀየር ያለውን የምግብ ብቃት እና የዕቃዎችን ደህንነት በመመሪያው መሰረት)
አስታውስ! ከእናንተ አንዱ መሣሪያዎችን በየወቅቱ በየ ሦስት ወር የሚፈትሽ ሃላፊ አድርጉ (ውኃውን መቀየር ያለውን የምግብ ብቃት እና የዕቃዎችን ደህንነት በመመሪያው መሰረት)
ቤትን መልቀቅ የሚያስገድድ ሁኔታ ከሆነ: የቤቱን ቁልፍ በፀጥታ ኃይሎች እጅ ማቆየት ይመረጣል (የሠፈር በአደጋ ጊዜ ሠራተኞችና / የማህበረሰብ ፖሊሲ)

በተጨማሪ: ለእያንዳንዱ የቤተሰብ አባል አንድ ትንሽ ሻንጣ መውሰድ ይመረጣል::

 • ልብስ + የውስጥ ልብሶች
 • ጫማ
 • የመጸዳጃ ቁሳቁሶች
 • ቢላዋ ለተለያዩ ጥቅሞች

ስለ ቤተሰብዎ ልዩ አስፈላጊ ነገሮች ያስቡ:

 • መሣሪያዎች እና የሕፃናት ምግብ
 • ጨዋታዎች እና ጋዜጦች
 • መጽሐፍት እና መጫወቻዎች

ከቤት ከመሄድ በፊት:

 • የኤሌክትሪክ ምንጮችን ማጥፋት
 • ጋዝን ቧንቧዎች መዝጋት
 • የውኃ ቧንቧዎችን መዝጋት
 • ቤትን መቆለፍ

የተሻሻለ ጥበቃ

በሲቪል የመከላከያ ሕግ 1951 መሰረት እያንዳንዱ ዜጋ በየቤቱ ወይም ፋብሪካ ውስጥ ሚቅላጥ (ወይም የመከላከያ መጠለያ ቦታ) ማዘጋጀት አለበት፡፡ ለዚህም ሲባል ፒቁድ ሃዖሬፍ የመጠለያዎችን እና ሚቅላጦችን ለማቋቋም የሚያስፈልጉ ደንቦችንና ዝርዝሮችን ውጥቷል፡፡
በተወሰኑ ሁኔታዎች ከሚቅላጥ ወይም ከመደበኛ መጠለያ ለየት ያሉ በአደጋ ወቅት መጠለያ ቦታዎችን ማዘጋጀት ፒቁድ ሃዖሬፍ ይፈቅዳል፡፡

የተጠበቀ መጠለያ ቦታን ማዘጋጀት

የጋራ መጠለያ - የሚያስፈልጉ መሣሪያዎች:

 • የሚሰራ መብራት የድንገተኛ መብራት ጨምሮ
 • ተገቢ መጸዳጃ ክፍል: የቧንቧ ውኃ እንዲሁም ተገቢ የውኃ ማጠራቀሚያ
 • ከትርፍ ዕቃዎች ነጻ
 • የመቀመጫ ቦታዎች

የመጠለያውን ሚቅላጥ ማዘጋጀት እና መቆጣጠር ሃላፊነት:

በቤቶች ኮሚቲ አባል ሃላፊነት መጠለያው በሁሉም ወቅት ለጥቅም ዝግጁ እንዲሆን መንከባከብና የመጠበቅ ሐላፊነት: በሃይፋ ከተማ ሃላፊነት- የህዝብ መጠለያዎችን የመጠበቅና የመጠገን ኃላፊነቱ የማዘጋጃ ቤት ነው፡፡ ባስፈለገ ደረጃ ደግሞ የሃይፋ ከተማ መጠለያዎች ዝግጁነትን ያስከብራል፡፡
በሕጉ መሰረት"የሚቅላጥ አያያዝ" ባለ መጠለያ ሰው በሙሉ መጠለያው ደረጃውን የያዘ ንጽህና እንዲኖረውና በአስፈለገ ጊዜ አገልግሎት ላይ መዋል አለበት::
ቤትን መልቀቅ የሚያስገድድ ሁኔታ ከሆነ: የቤቱን ቁልፍ በፀጥታ ኃይሎች እጅ ማቆየት ይመረጣል (የሠፈር በአደጋ ጊዜ ሠራተኞችና / የማህበረሰብ ፖሊሲ) በተጨማሪ: ለእያንዳንዱ የቤተሰብ አባል አንድ ትንሽ ሻንጣ መውሰድ ይመረጣል::
 • ልብስ + የውስጥ ልብሶች
 • ጫማ
 • የመጸዳጃ ቁሳቁሶች
 • ቢላዋ ለተለያዩ ጥቅሞች
 • ስለ ቤተሰብዎ ልዩ አስፈላጊ ነገሮች ያስቡ:

 • መሣሪያዎች እና የሕፃናት ምግብ
 • ጨዋታዎች እና ጋዜጦች
 • መጽሐፍት እና መጫወቻዎች
 • ከቤት ከመሄድ በፊት:

 • የኤሌክትሪክ ምንጮችን ማጥፋት
 • ጋዝን ቧንቧዎች መዝጋት
 • የውኃ ቧንቧዎችን መዝጋት
 • ቤትን መቆለፍ

በመሬት መንቀጥቀጥ እለት ምን ማድረግ እንዳለባችሁ እንዴት ታውቃላችሁ?

በመሬት መንቀጥቀጥ እለት እርግጠኛ ክፍት ቦታ መሆን አለበት!

በተገነባ ቦታ ላሉ ሰወች መመሪያ በመሬት መንቀጥቀጥ ወቅት ቤት ወይም በህንጻ ውስጥ ካላችሁ: ወደ ተጠበቀ ቦታ እንደ ቅደም ተከተሉ ሂዱ:
 • ክፍት ነጻ ቦታ መውጣት- ከተቻለ ወደ ክፍት ቦታ ውጡ (በተወሰኑ ሰከንድ ውስጥ)
 • የተጠበቀ መጠለያ (ማማድ) ወይም ደረጃዎች ስር- ባስቸኳይ መውጣት የማይቻል ከሆነ፤ማማድ ውስጥ ግቡ በሩን ኝ አፅጉ:: ማማድ ከሌለ ደረጃዎች ስር ግቡ፤ ከተቻለ ወጥታችሁ ከህንጻው ራቁ፡፡
 • ‭መውጣት/መጠለል የማይቻል ከሆነ፤ ከባድ ጠረበዛ ስር ወይንም ውስጣዊ ክፍል ኮርነር መጠጋት ይመረጣል- ግዚፍ የቤት ዕቃ ስር ወይም ወልወል ላይ ራሳችሁን በእጃችሁ አፍናችሁ ተቀመጡ፤ በተሽኮልኳይ ወንበር ተጠቃሚ ከሆናችሁ፤ ጎማውን ቆልፋችሁ ራሳችሁን በእጃችሁ ሸፍኑ፡፡

ክፍት ሜዳ ቦታ ላይ ለሚገኙ መመሪያዎች፡

ክፍት ቦታ - በጣም የተጠበቀ ቦታ!
 • ክፍት ቦታ በተቻለ መጠን ከሕንጻዎችና የኤሌክትሪክ አስተልላላፊ ግንዶች ራቁ፡፡
 • ከወዳቂ ዕቃዎች ተጠንቀቁ (የግድግዳ ድንጋዮች ማዝጋን የጠርሙስ ስባሪ የኤሌክትሪክ ኬብሎች ወዘተ)
ማወቅ ያስፈልጋል: በመሬት መንቀጥቀጥ ጊዜ በመሬት በታች በሚገኙ መጠለያ ሚቅላጥ ውስጥ መቆየት የለም!

መኪና ውስጥ ላሉ መመሪያዎች:

 • ወዲያውኑ መክናውን አቁመው መንቀጥቀጡ እስኪያቋርጥ ድረስ ተሽከርካሪው ውስጥ ይጠብቁ - መኪናው እርስዎን ይከልለወታል!
 • ድልድይ ላይ/ሥር ፤ ሕንጻዎች አቅራቢያ; ቁልቁለት፤ የኤሌክትሪክ አስተልላላፊ ግንዶች አጠገብ ላይ መኪናውን አያቁሙ አያቁሙ::

ቤትን እና ቤተሰብን ማመዘጋጀት:‬

በመሬት መንቀጥቀጥ ወቅት የሚደርሱ ቁስለት ጉዳቶች አብዛኛወቹ ከባድ ዕቃ መደርደሪያዎች በመሰባበር፤ የተሰባበረ ጠርሙስ፤ እሳት ቃጠሎ እና ጋዝ ናቸው:: ስለዚህ:
 • የመጻሕፍት የመደርደሪያ: የተሰቀሉ ቴሌቪዥኖችን ዕቃወችን ከግድግዳዎች ማጠናከር
 • የሚከተሉት ዕቃዎች ካሉበት መጥበቃቸውን ያረጋግጡ: የፀሐይ የውሃ ማሞቂያ: የጋዝ ታንኮችና: ማዝጋንን::
 • ነዳጅና መርዛማ ነገሮች በተቆለፈና ከሙቀት በራቀ ቦታ ያስቀምጡ
 • ከባድ ነገሮችን አነስተኛ ቦታ ያስቀምጡ
 • ስለ መሬት መንቀጥቀጥ ለቤተሰብ ልምምድ ያድርጉ
 • መሽሎኪያውን፤የሃሽማል ማብሪያና ማጥፊያ፤ የጋዝና ውሃ ቦታወች ለልጆች ያስተምሩ
 • አስተማማኝ የመገባኛ ቦታ ያዘጋጁ

ከመሬት መንቀጥቀጥ በኋላ ትክክለኛ ባህሪ:

 • ማንኛውም ዓይነት እሳት (በሞባይል ስልክ አጠቃቀም ጨምሮ)የጋዝ ፍሳሽ ፍንዳታ ሊያስከትል ስለሚችል::
 • ከሕንፃ በመውጣት ክፍት ቦታ ከሕንፃዎች ራቅ በማለት ቆዩ
 • ሕንጻውን ለቃችሁ ከመሄዳችሁ በፊት የጋዝ እና የኤሌክትሪክ ምንጮችን ዝጉ:: የሕንጻውን ጋዝ እና ኤለክትሪክ የሚያድስ ባለ ሙያ ብቻ ነው::
 • የሕንጻው ማሃንዲስ ካልፈቀደ ወደ ተጎዱት ሕንጻዎች መግባት ክልክል ነው (ርዳታ ለማበርከትብቻ ካልሆነ)
 • መረጃ እና መመሪያዎችን ለማግኘት በብዙኃን የመገናኛ አውታሮች አዳምጡ::
 • ለተጨማሪ መንቀጥቀጥ ዝግጁ ይሁኑ ተጨማሪ መንቀጥቀጥ ከትንሽ ደቂቃዎች አንስቶ እስከ ቀናት ለከሰት ይችላል: በመጀመሪያው መንቀጥቀጥ የተጎዱ ህንጻዎችን ሊያፈር ስይችላል::

በፈረሰው ለተደፈኑ ሰወች፡‬

 • በአቅራቢያችሁ ፍርስራሽ ስር የተቀበረ ሰው ካለ ባላችሁ ዘዴ እና መሳሪያ ተጠቅማችሁ እርዳታ አቅርቡለት: ለምሳሌ ከባድ ብረትና በመኪና ማንሻ: ቤት ውስጥ በሚገኙ መሳሪያወች::
 • ‭የመጀመሪያ እርዳታ አቅርቡ
 • እናንተ ፍርስራሹ ስር ከሆናችሁ ራሳችሁን ለማዳን ሞክሩ
 • አፍና አፍንጫችሁን በጨርቅ አቧራ እንዳይገባ ሸፍኑ እና ድካም እንዳያሸንፋችሁ፤ ሁኔታችሁን ተከታተሉ
 • ከደረሳችበት ቧንቧም ሆነ ግድግዳ ያላችሁበት ቦታ እንዲታወቅ በድንጋይ አንኳኩ ወይንም በፊሽካ ንፉ
 • እሳት አታንድዱ
በመሬት መንቀጥቀጥ ወቅት - እርግጠኛ ክፍት ቦታ

በሚሳይል ጥቃት ወቅት ምን ማድረግ እንዳለባችሁ እንዴት ታውቃላችሁ?

ከሮኬቶች እና ከሚሳይሎች መከላከል

የሚስማማህን የተጠበቀ መርጠህ የማንቂያ ድምጽ ከተሰማ ጀምሮ መጠለያ ለመግባት 60 ሰከንድ ነው::

የሃይፋ ማስተንቀቂያ ክፍለ ከተማ

ሃይፋ ከተማ - ሃይፋ 75 ቅሪያት ሃይም እና ሽሙኤል - ቅራዮይ 70 የያይፋ ባህረ ሰላጤ - ሃይፋ 78 ናኦት ቴሬስ - ሃይፋ 79

ህይወት አዳኝ መመሪያዎችን በጥሞና ይከታተሉ!

ከአደጋ መጠለያ ቦታዎችን ምርጫ መመሪያ፡ ተስማሚ የተጠበቀ ከአደጋ መጠለያ ቦታ መርጠህ የማንቂያ ድምጽ ከተሰማ ጀምሮ መጠለያ ለመግባት 60 ሰከንድ ነው::
 • በማማድ (የቤት በአደጋ ወቅት መጠለያ) ወይም ማማቅ (የፎቅ መጠለያ) በቶሎው -መጠለያ ግቡ የብረት መስኮትና በር ዝጉ
 • ሚቅላጥ: በጋራ ቤቶች የሚገኝ መጠላየ ሚቅላጥ በደረጃወች አንስቶ መግባት የሚቻል ከሆነ ብቻ: ህዝባዊ ሚቅላጥ በተወሰነው ጊዜ መድረስ የሚቻል ከሆነ ብቻ::
 • በማማድ (የቤት በአደጋ ወቅት መጠለያ) ወይም ማማቅ (የፎቅ መጠለያ) ወይም ሚቅላጥ በሌለ ቦታ፡ 3ኛ ፎቅ ያለው ህንጻ መጨረሻ ፎቅ የሚኖሩ ማማድ/ማማቅ/ሚቅላጥ ከሌለው ሁለተኛ ፎቅ ወርደው ደረጃው ስር ይጠለሉ፡፡ 3ኛ ፎቅ ያለው ህንጻ የሚኖሩ ማማድ/ማማቅ/ሚቅላጥ ከሌለው አንድ ፎቅ ወርደው ደረጃው ስር ይቆዩ
 • ማማድ/ማማቅ/ሚቅላጥ ወይም ውስጣዊ ደረጃ ከሌለው፡ ወለል ላይ ተቀመጡ (መስኮት መስመር በታች) ውስጣዊ ክፍል (በተቻለ መጠን በደቡብ አቅጣጫ) ግድግዳ ዳር መስኮት ፊት ለፊት እንዳይሆን ወይም መታጠቢያ ክፍል: መጸዳጃ ቤትም መምረጥ ይቻላል፡፡

ከህንጻ/ፎቅ ውጭ

 • በተገነባ አካባቢ- ወደ ቤት/ህንጻ ገብታችሁ መመሪያውን ተከታተሉ፤ ቤቶች መግቢያ መገኘት ከሚተኮሱት የሚሳየልና ሮኬት ተፈናጣሪ ሊያጋጥም ስለሚችል አደገኛ ነው፡፡
 • በክፍት ቦታ- መሬት ላይ በሆዳችሁ ተኝታችሁ ራሳችሁን በእጃችሁ ሸፍኑ፤ በድንገተኛ ጊዜ የፎቁን በር ከፍታችሁ ተውት ውጭ ላለ ሰው እንዲሆን::

መኪና ውስጥ ለሚገኙ:

 • በጥንቃቄ መኪናውን በጎዳና ዳርአቁሙ
 • ከመኪና ወጥታችሁ መጠለያ ቦት ግቡ
 • መጠለያ ከሌለ መሬት ላይ በሆዳችሁ ተኝታችሁ ራሳችሁን በእጃችሁ ሸፍኑ

ማወቅ ያስፈልጋል: የፒቁድ ሃኦሬፍ ስልክ ሞቄድ 104
ሌላ መመሪያ ከሌለ ከ10ደቂቃ በኋላ ከመጠለያ መውጣት ይቻላል ከማይታወቁ ቁሳቁሶች መራቅ ይመረጣል:: በአካባቢያችሁ የወደቀ ሮኬት የማይታወቅ ነገር ካያችሁ: ገምጋሚው ሰው ከቦታው አርቃችሁ ለመከላከያ ሃይል አስተላልፉ::

ቃጠሎ በተነሳ ጊዜ ምን ማድረግ እንዳለባችው እንዴት ያውቃላችሁ?

ቃጠሎ በተነሳ ጊዜ ምን ማድረግ አለ:

 • የእሳት አደጋን በቅድሚያ ጥሩ (102 በሁሉም ስልክ)
 • ባላችሁ መሳሪያ ሁሉ እሳቱን ለማጥፋት ሞክሩ ( በውሃ: በባልዲ ውሃ: በመወልወያ: በሌላም)
 • ተቀጣጣይ የሆኑ ነገሮችን በሙሉ ከቃጠሎው አካባቢ አርቁ
 • ቤተሰባችሁ በሙሉ ከቦታው መውጣታቸውን አረጋግጡ
 • ለቤተሰባችሁ ለድንገተኛ ጊዜም የመገናኛ ቦታ ወስኑ
 • ቃጠሎው ከአቅማችሁ በላይ ከሆነ ከቦታው ወጥታችሁ ጎረቤትን ፎቁ እንዲለቁ ንገሯቸው
 • ቃጠሎው ተፋፉሞ ጢሱ በዝቶ ከክፍሉ ውጭ አላስወጣችሁ ካለ: ካላችሁበት ሁናችሁ ተጎንበሱ ያለውን መሰኮትና ቀዳዳ ሁሉ ዝጉ (ይህ ዘዴ ጢሱ ወደ ክፍሉ እንዳይገባ እንዲታገድ ነው)
 • ወደ ውጭ አቅጣጫ የሚከፈት መስኮት ካለ: ወደላይ ወደመስኮቱ የሚጥለቀለቅ ጢስ ከለለ : መስኮቱን ከፍታችሁ ንጹህ አየር አስገቡ: (ወደመስኮቱ የሚዘልቅ ጢስ ካለ መስኮት አይከፈትም)
 • ያላችሁበትን ቦታ ባስቸኳይ ለማሳወቅ ሞክሩ
ወደ ሃሽማልና የኤሌክትሪክ መሳሪያዎች ውሃ መርጨት ክልክል ነው

አደገኛ ፈሳሽ ነገሮች በፈሰሱ ወቅት ምን ማድረግ እንዳለባችሁ እንዴት ታውቃላችሁ?

አደገኛ ፈሳሽ ነገሮች በፈሰሱ ወቅት መደረግ ያለበት፡

 • ወደ ቤት ገብታችሁ መስኮትንና በርን ዝጉ
 • የማሞቂያ እና የማብሰያ ታኑርን ዝጉ፤ ማዝጋንና ማናፈሻ ቀዳዳወችን: የውሃ እና የጋዝ ቧንቧን በሙሉ ዝጉ
 • ለመጠለያ ክፍል ግቡ: ያለውን በር: መሰኮትና ቀዳዳ ሁሉ ዝጉ: ክፍሉን ማሞቅ እና እሳት ማንደድ ክልክል ነው??
 • ከቤት ውጭ ለሚገኙ- በቶሎው ወደ ተጠበቀ ቦታ ግቡ
 • በመኪና ላይያሉ- ያለውን በር: መሰኮትና ቀዳዳ ሁሉ ማዝጋንም ዝጉ:በመገናኛ ዘዴዎችበሚነገረው መሰረት በጥንቃቄ መንገዳችሁን ቀጥሉ::
 • የአደገኛው ፈሳሽ የህመም ምልክቶች እንደ የራስ ህመም: መጠውለግ: የትንፋሽ እጥረት: ዓይንንእና አፍንጫን እሽት ከተከሰቱ: የተነካውን አካባቢ በውሃ አጥቦ ለተመልካች ሃኪም ማስተላለፍ ነው::
 • በሜዲያ የሚነገሩትን መመሪያ ተከታተሉ
 • ድርጊቱ ሲከወን ቤቱን በአየር ያናፍሱት
የአደገኛ ፈሳሽ ንጥረ ነገሮች በተከሰተ ጊዜ ዋናው አስፈላጊ እርምጃ: አንድ ቦታ መዝጋትና ማዝጋንን ማጥፋት:: ከውጭ ያሉ- ወደ ውስጣዊ ክፍል ይግቡ:: ከውጭ ከመሆን ከውስጥ መሆን ይመረጣል::

ሱናሚ ቢመጣ ምን ማድረግ አለብን?
ሱናሚ ምንድን ነው?

ሱናሚ ምንድን ነው?

የሱናሚ ማዕበል በባህር ውስጥ በሚነሱ በጣም ረዣዥም ሞገዶች አብዛኛውን ጊዜ በመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት የሚነሳ ማዕበል ነው:: ማዕበሎቹ ጥልቀት ወደሌለበት ስፍራ ሲገቡ:ወደላይ በመወርወር በባህር ዳርቻው በከፍተኛ ኃይል ሊመቱ ይችላሉ:: የሱናሚ ሞገዶች ሂደታቸው ረዥም ጊዜ ሊሆ ን ይችላል ሆኖም የመጀመሪያው ሞገድ ግዙፍ ላይሆንና ከባድ አደጋ ላያደርስ ይችላል::

የሱናሚ ሞገድ መቀስቀሱንና መቅረቡን የሚያሳዩ ምልክቶች:

 • ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ
 • ድንገተኛ የባህር ውሃ ከደንብር መሸሸት / ወይም ከባሕር የሚመጣ ከፍተኛ ድምጽ
 • የሱናሚ መቅረብ ምልክቶች ሲታወቅ ምን ማድረግ ይገባል?

  • የመሬት መንቀጥቀጥ በሚከሰትበት ወቅት በባህር ዳርቻ ላይ ከተገኙ ወይም ድንገተኛ ማስጠንቀቂያ ሲሰሙ: የባህርን ዳር ሱነሚው ጎርፍ ሳያጥለቀልቀው በቶሎው ከቦታው ይራቁ::
  • ቢያንስ ቢያንስ ከአንድ ኪሎሜትር ካላነሰ ርቀት ከባህርመራቅ: ወይም ካርሜል ተራራ መውጣት: ወይም ወደ ደህና ቦታዎች / ምልክት ያላቸው መሰብሰቢያ ቦታዎች (እነዚህ ቦታዎች ከአደጋ ውጭ ናቸው(
  • የባህር ዳርቻውን ለቀው መሄድ ያልቻሉ ቢያንስ በአቅራቢያ ባለ ህንጻ ላይ ወደ አራተኛ ፎቅ ይውጡ::
  • ተሽከርካሪ አይነዱ: ለድንገተኛ አደጋ ፈጥኖ ደራሽ ሃይሎች/ ለማመለሻ ትራንስፖርቶች መንገዶችን ይልቀቁ::
  • የመሬት መንቀጥቀጥ ከተከሰተ ጊዜ ጀምሮ በ 12 ሰዓታት ውስጥ ወደ ባሕር ዳርቻ አይመለሱ::
  • መመሪያ ለማግኘት ሚዲያን ያዳምጡ::
  • ምልክቶቹን በደንብ ይወቁ:

  መንፈሳዊ ጭንቀት ላደረባቸው የመጀመሪያ እርዳታ ማቅረብ እንዴትአርጋችሁ ታውቃላችሁ?

  ለለየት ባሉ ሁኔታዎች ከከፍተኛ ውጥረት መቆጠብ ይሻላል::

  "አስፈሪ ወይንስ አደገኛ" ብሎ መመርመር: ያላችሁበት ሁኔታ አደገኛ ነው ወይስ ፍርሃት ብቻ? ስጋትን ለማቃለል ከታሰበ እንደሚከተለው ይሆናል:

  መሰረታዊ ሰብአዊ ስሜትንና አስፈላጊ ድጋፎችን አበርክቱ

  • ምግብ እና መጠጥ በወቅቱ ተመገቡ (ጣፋጭ ነገሮችንም) በቂ የምኝታ ጊዜ
  • ውስጣዊ ስሜታችሁን ሳትደብቁ ብስጭት: ሳቅ: ለቅሶ: ፍቅርና መከፋትን በጋሃድ አሳዩ
  • ትንፋሻችሁን በማደራጀት ለመረጋጋት ሞክሩ

  ሁኔታውን ሰብሰብ አድርጎ መስመር ማስያዝ

  • በቶሎው ወደ መደበኛ ፕሮግራሞች ለመመለስ ሞክሩ
  • በተቻለ መጠን ቤተሰብን በፕሮግራም አሳትፉ:

  እውነተኛና አዲስ መረጃዎችን ፈልጉ

  • እውነተኛ መረጃ ካገኛችሁ በኋላ ለቤተሰብ አማክሩ ለያንዳንዱ እንደ እድሜው፤
  • ስህተትን ለመበተን ከደህንነት ሃላፊዎች ጋር ግንኙነት አድርጉ (የማህበረሰባዊ ፖሊስ/ የድንገተኛ የሰፈር ሰራተኞች)

  የአስፈላጊነትን ስሜት አጠንክሩ

  • ልጆቻችሁ ጎን አትለዩ አጠናክሯቸው
  • ስለድርጊቱ ከቤተሰብ ጋር ተወያዩ
  • የተዋጣችሁበትን መንገድ: በህይወታችሁ ያሳለፋችሁትን አካፍሉ
  • ከቤተዘመዱ ጋር ግንኙነት መስርቱ
  • ጊዜ ካላችሁ ድጋፋችሁን ለሌሎች አበርቱ
  አዎንታዊ አመለካከት መያዝና ተስፋ አለመቁረጥ አስፈላጊ ነው ሁኔታው ካልተሻሻለ ከባለሙያ ጋር መማከር ይሻል መንፈሳዊ ጭንቀት ላደረባቸው የመጀመሪያ እርዳታ ማቅረብ እንዴት አርጋችሁ ታውቃ

  የፀጥታ ኃይል ድርጅቶች

  በእውነተኛ ወቅት ዝግጁና አመች እንዲሆንላችሁ: አስፈላጊ የስልክ ቁጥሮችንና ቅድመ ዝግጅት የሚያስፈልጋቸውን ቁም ነገሮች በዝርዝር አዘጋጅተንላችኋል::

  ፍሪጅደር ላይ አጣብቁ